1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
አዲስ የተሾሙት የካቢኔ አባላት እነማን ናቸው?
November 1,2016

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ በአዲስ መልክ ያደራጁት ካቢኔ
አዳዲስ አባላት ሹመትን ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው አስፀድቀዋል።
admin@hebrezema.info
1
የኢፌዴሪ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስትር

አቶ ታገሰ ጫፎ

ብሔር፦ ጋሞ

የትምህርት ዝግጅት

- በስነህይወት ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ (BSC) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣
- ማስተርስ ዲግሪ (MSC) በአሳ ሳይንስና እርባታ ከህንድ ሀገር፣
- የማስተርስ ዲግሪ (MBA) በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ኦፖን ዩኒቨርሲቲ፣

ዋና ዋና የስራ ልምዶች

- በወረዳ አመራርነት ለሁለት አመታት፣
- በዞን አመራርነት ለስድስት አመታት፣
- የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር፣
- የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣
- የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ በድምሩ በክልል አመራር ደረጃ ለ10 አመታት፣
- ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ የኢፌዴሪ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

ከላይ በተጠቀሱት የስራ ጊዜያት የከተማና የገጠር ኢንቨስትመንት በክልሉ ለማስፋፋት ስኬታማ አስተዋፅኦ በማድረጋቸው የክልሉ የንግድ ሪፎርም ፓኬጅ በተሟላ ሁኔታ እንዲደራጅ
አደርገዋል። የመንግስት የሪፎርም ስራዎች የስራ ሂደት ለውጥ አመራር በተሻለ ሁኔታ እንዲፈፀም የጎላ አስተዋፅኦ በማድረጋቸው፤ በክልሉ የፍትህ ዘርፍ ስራዎች የመልካም አስተዳደር
ፓኬጅ ዝግጅት በተሻለ ስለመሩ በፌዴራል ስራ የመልካም አስተዳደርና የሌሎች ጥናቶች በጥልቀት እንዲጠኑ በማስተባበራቸውና ውጤታማ ሆነዋል።

የኢፌዴሪ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር

ዶ/ር አብርሃም ተከስተ

ብሔር፦ ትግራይ

የትምህርት ዝግጅት

- የመጀመሪያ ዲግሪ (BA) በኢኮኖሚክስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣
- ማስተርስ ዲግሪ (MA) በኢኮኖሚክስ ፖሊሲ አናሊሲስ፣
- ዶክትሬት ዲግሪ (PHD) በኢኮኖሚክስ ከእንግሊዝ ሀገር፣

ዋና ዋና የስራ ልምዶች

- ከ1983-1991 ዓ.ም ከጀማሪ እስከ ከፍተኛ ኢኮኖሚስት በቀድሞ የኢኮኖሚ ልማትና ትብብር ሚኒስቴር፣
- ከ1996-1998 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባው ዋና አማካሪና የከንቲባ ፅ/ቤት ኃላፊ፣
- ከ1998-2003 ዓ.ም የስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የፖሊሲ፣ ጥናትና እቅድ ቢሮ ኃላፊ፣
- ከ2003-2008 ዓ.ም የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ፣
- ከ2008 ዓ.ም መጀመሪያ ጀምሮ በብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሲሆኑ፣

አንደኛውንና ሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዝግጅት ውስጥ ጉልህ ተሳትፎ በማድረግ የአገሪቱን ማክሮ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን በመከታተል መንግስትን በማማከርና
ለህዝቡ በማሳወቅ ውጤት ያስገኙ የሀገሪቱ የበጀት ስርዓት በውጤት ላይ ተመስርቶ የፕሮግራም በጀት ስርዓት እንዲሸጋገር በማድረግ፤ አገራዊ የከተማ ልማት እና መልካም
አስተዳደር ፕሮግራሞችን በዝርዝር በማዘጋጀትና ወደ ትግበራ እንዲሸጋር በማድረግ በከተማና ቤቶች ፕሮግራም የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት የወጣቶች ልማት
ፕሮግራም በከተሞ መሰረተ ልማት ፕሮግራም ውጤት እንዲገኝ የጎላ አስተዋፅኦ አድርገዋል።

የኢፌዴሪ እርሻና፣ የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር

ዶ/ር እያሱ አብርሃ

ብሔር፦ ትግራይ

የትምህርት ዝግጅት

- የመጀመሪያና ማስተርስ ዲግሪያቸውን በአግሮኖሚ በማዕረግ ከራሺያ ሳብ ትሮፒክስ ኢንስቲትዩት፣
- ፒ.ኤች.ዲ (PHD) በእፅዋት ሳይንስ ከቼክ ሪፐብሊክ ፕራግ ዩኒቨርሲቲ፣

ዋና ዋና የስራ ልምዶች

- ከ1986-1993 ዓ.ም ድረስ በትግራይ ምዕራባዊ ዞን የዞን ኤክስቴንሽን ኃላፊ አግሮኖሚስት፣
- ለ1994-1995 ዓ.ም የትግራይ ግብርና ቢሮ የአዝርዕት ክፍል ኃላፊ፣
- ከ2001-2003 ዓ.ም ድረስ የመቐለ እርሻ ምርምር ኃላፊና ተመራማሪ፣
- ከ2004 ዓ.ም እስከ አሁን የትግራይ የእርሻ ምርምር ዋና ዳይሬክተር፣

በመሆን የሰሩ ሲሆኑ በዘርፉ በምርምር ስራቸው ውጤት ያስመዘገቡ ናቸው።

የኢፌዴሪ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ሚኒስትር

ፕ/ር ፍቃዱ በየነ

ብሔር፦ ኦሮሞ

የትምህርት ዝግጅት

- በእንስሳት ሳይንስ (BSC) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣
- ማስተርስ ዲግሪ (MSC) በእንስሳት እርባታ ከሃረማያ ዩኒቨርሲቲ፣
- ፒ.ኤች.ዲ (PHD) በደሪ ቴክኖሎጂ ከነርዌይ የግብርና ዩኒቨርሲቲ፣
- የትምህርት ማዕረግ የምግብ ሳይንስት ቴክኖሎጂ ፕሮፌሰር፣

ዋና ዋና የስራ ልምዶች

- ከ1975-1987 ዓ.ም ድረስ በረዳት ሌክቸረርነት፣ በሌክቸረርነትና በትምህርትና በምርምር ስራ ተሳትፈዋል፡፡
- ከ1988-1991 ዓ.ም ድረስ የአዋሳ ግብርና ኮሌጅ ምክትል ዲን፣
- ከ1992-1998 ዓ.ም ድረስ በቀድሞ የደቡብ የአሁኑ ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክስ ጉዳዮች ኃላፊ፣
- ከ1998-2008 ዓ.ም ድረስ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣
- ከ2008 ዓ.ም መጀመሪያ ጀምሮ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሲሆኑ፣

ከላይ በተጠቀሱት የስራ ዘመናት ከአርባ አምስት በላይ ፅሁፎችን በግልና በቡድን በታወቁ ጆርናሎች ያሳተሙ፤ በዩኒቨርሲቲ መምህርነት፣ በተመራማሪነትና በዩኒቨርሲቲ አመራርነት
ባገለገሉባቸው ቦታዎች ውጤት በማስመዝገብ የታወቁ፣ በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ በተደጋጋሚ ዩኒቨርሲቲው በስራ አፈፃፀም ከአቻዎቹ ግንባር ቀደም እንዲሆን
ያበቁ፣ በተለያዩ የዩኒቨርሲቲ አመራር ቦታዎች በኮሚቴ አመራርነትና ሰብሳቢነት የሰሩ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ኮነሰርተም በሊቀ-መንበርነት በመምራት ላይ የነበሩ ናቸው።

የኢፌዴሪ ንግድ ሚኒስትር

ዶ/ር በቀለ ቡላዶ

ብሔር፦ ሲዳማ

የትምህርት ዝግጅት

- የመጀመሪያ ዲግሪ (BA) በማኔጅመነት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣
- ማስተርስ (MBS) በቢዝነት ሳይንስ፣
- ፒ.ኤች.ዲ (PHD) በስትራቴጂክ ማኔጅመንትና ቢዝነስ ፖሊሲ ከ(NUI) አየርላንድ ከሚገኝ ዩኒቨርሲቲ፣
- የአካዳሚክ ማዕረጋቸው በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር፣


ዋና ዋና የስራ ልምዶች

- ከ1985-1987 ዓ.ም ኢትዮጵያ አየር መንገድ የግዥ ባለሙያ በመሆን ሰርተዋል፣
- ከ1987-1989 ዓ.ም የወንዶ ንግድ ኩባንያ ኃላፊ፣
- ከ1993-1995 ዓ.ም የሞሃ ለስላሳ መጠጥ ኢንዱስትሪ የፔፕሲ ዘርፍ የገበያና ሽያጭ ኃላፊ፣
- ከ1996-2000 ዓ.ም የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ የፕላንና የቢዝነስ ልማት ክፍል ኃላፊ፣
- ከ2000-2008 ዓ.ም ድረስ የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት፣
- ከመጋቢት 2008 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሲሆኑ፣

በመንግስት የተለያዩ ተቋማትና በግል ኩባንያዎች በከፍተኛ ባለሙያነት፣ በመምህርነትና በአመራርነት በመሩባቸው ጊዜያት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ በተማሪዎቻቸውና
በሰራተኞቻቸው የተመሰገኑና መልካም ስነ ምግባርና የረዥም ጊዜ ልምድ ያካበቱ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የኢፌዴሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር

ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ

ብሔር፦ ኦሮሞ

የትምህርት ዝግጅት

- የመጀመሪያ ዲግሪ (BSC) ኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣
- የማስተርስ ዲግሪ (MSC) በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣
- ፒ.ኤች.ዲ (PHD) በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ዱላቡርግ ኤሲን ዩኒቨርሲቲ ጀርመን፣

ዋና ዋና የስራ ልምዶች

- በሌክቸረርነት በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ዲፓርትመንት ኃላፊነት አገልግለዋል፣
- በጀርመን ዩኒቨርሲቲ በተመራማሪነት ሰርተዋል፣
- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ፋክሊቲ ዲን በመሆን አገልግለዋል፣
- በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በዳይሬክተር ጄነራልና በሚኒስቴር ዴኤታነት አገልግለዋል፣

ከ11 የሚልቁ በግል በቡድን ፅሁፎችን በታወቁ አለም አቀፍ ጆርናሎች ያሳተሙ የተሰጣቸው ስራ በትጋት በታማኝነትና በቅንነት በመስራት ውጤት በማስመዝገብ የሚታወቁ መልካም
ስነ ምግባር ያላቸው ናቸው።

የኢፌዴሪ ትራንስፖርት ሚኒስትር

አቶ አህመድ ሺዴ

ብሔር፦ ሶማሌ

የትምህርት ዝግጅት

- ፖስት ግራጁዌት ዲፕሎማ፣ በገጠር ሀብት ማኔጅመነትና ግጭት አወጋገድ፣ የማህበራዊ ጥናት ኢንስቲትዩት፣ ዘሄግ ኔዘርላንድ፣
- ባችለር ዲግሪ በኢኮኖሚክስ ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ፣
- ማስተርስ ዲግሪ በህዝብ ተሳትፎ፣ ልማትና ማህበራዊ ለውጥ ሳሴክስ ዩኒቨርሲቲ ብራይተን ዩናይትድ ኪንግደም፣
- ማስተርስ ዲግሪ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን፣ ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ ለንደን ዩናይትድ ኪንግደም፣

ዋና ዋና የስራ ልምዶች

- ከታህሳስ 1990 መስከረም 1991 ዓ.ም በሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሲኒየር ኢኮኖሚስት፣
- ከመስከረም 1991 ዓ.ም እስከ ግንቦት 1994 ዓ.ም በሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ፣
- ከመጋቢት 1995 ዓ.ም እስከ መስከረም 1996 ዓ.ም በሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የአርብቶ አደርና ገጠር ልማት ኮሚቴ ሊቀ-መንበር፣
- ከመስከረም 1996 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 1997 ዓ.ም በሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የፕሬዝዳንቱ ፅ/ቤትና የካቢኔ ፅ/ቤት ኃላፊ፣
- ከጥቅምት 1997 ዓ.ም እስከ መስከረም 1998 ዓ.ም በሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ቢሮ ኃላፊ፣
- ከመስከረም 1998 ዓ.ም እስከ መጋቢት 2001 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሱማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ፣
- ከመስከረም 1998 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 2001 ዓ.ም በሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የአርብቶ አደርና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ፣
- የሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የፕሬዝዳንቱ ከፍተኛ የልማት አማካሪ፣
- የሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርናና ገጠር ልማት ምክትል የቢሮ ኃላፊ
- ከህዳር 2001 ዓ.ም ጀምሮ የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን፣

ለእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ስኬት የሚያስፈልግ የውጭ ሀብትን በብዛትና በጥራት ለማሰባሰብ እንዲሁም የተገኘውን ገንዘብ ለታለመለት የትኩረት መስክ እንዲውል ለማድረግ
ለጋሾችን፣ አስፈፃሚ አካላትንና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በመምራትና በማስተባበር በአገር አቀፍ ደረጃ ለተገኘው የልማት ውጤት አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡ በሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ
መንግስት ውስጥ ያሉ ልዩ ልዩ ተቋማትን በመምራት፣ የክልሉን ልማት በማረጋገጥ፣ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን የሚያግዙ ጥረቶችን በማስተባበርና የተቋማትን አቅም ግንባታ
ስራዎችን በመምራት እንዲሁም የኢትዮጵያ ሱማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የስራ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ ክልሉ ላስገኘው ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ
አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡


የኢፌዴሪ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር

ዶ/ር አምባቸው መኮንን

ብሔር፦ አማራ

የትምህርት ዝግጅት

- የመጀመሪያ ዲግሪ (BA) በኢኮኖሚክስ ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣
- ሁለተኛ ዲግሪ (MA) በፐብሊክ ፖሊሲና ኢኮኖሚክስ ከደቡብ ኮሪያ KDI School of Public Policy and Management
- ማስተርስ ዲግሪ (MSC) በዓለም አቀፍ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት እንግሊዝ ሀገር ከሚገኘው ኬንት ዩኒቨርሲቲ፣
- ፒ.ኤች.ዲ (PHD) በኢኮኖሚክስ እንግሊዝ ሀገር ከሚገኘው ኬንት ዩኒቨርሲቲ፣

ዋና ዋና የስራ ልምዶች

- ከ1983-1987 ዓ.ም ድረስ የወረዳ አመራር፣
- ከ1990-1993 ዓ.ም የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ኃላፊ፣
- ከ1994-1997 ዓ.ም የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅ/ቤት ኃላፊ፣
- ከ1998-1999 ዓ.ም የአማራ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ፣
- ከ2004-2005 ዓ.ም የአማራ መልሶ መቋቋምና ልማት ድርጅት (አመልድ) ዋና ዳይሬክተር፣
- ከ2006-2007 ዓ.ም የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣
- ከ2008 ዓ.ም መጀመሪያ ጀምሮ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን፣

ዶ/ር አምባቸው የትጥቅ ትግሉን በመቀላቀል ደርግን ለመደምሰስ በተደረገው ትግል አስተዋፅኦ በማበርከት ከመልሶ ማደራጀት ጀምሮ በሽግግሩ ዘመን የወረዳ አመራር በመሆን ህዝቡን
በማረጋጋት አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡ በተለያዩ ጊዜያት በድርጅትና በመንግስት እንዲሁም ክልሉን መልሶ በማደራጀት ተቋማት ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞች እንዲተገበሩ በመምራትና
በማስተባበር ስኬታማ ስራዎችን ሰርተዋል፡፡ የከተማ ልማት ኢንቨስትመንትና የኢንዱስትሪ ስራዎች በክልል ላስገኙት ውጤቶች አስተዋፅኦቸው ነበረበት፡፡ ከስድስት በላይ የምርምር
ፅሁፎች በህትመትና ኤሌክትሮኒክስ ጆርናሎች አሳትመዋል።

የኢፌዴሪ ኮንስትራክሽን ሚኒስትር

ኢ/ር አይሻ መሀመድ

ብሔር፦ አፋር

የትምህርት ዝግጅት

- የመጀመሪያ ዲግሪ በሲቪል ምህንድስና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ፋካልቲ፣
- ማስተርስ ዲግሪ በለውጥና ትራንስፎርሜሽናል ሊደርሺፕ ከግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ ኢንግላንድ፣

ዋና ዋና የስራ ልምዶች

- ከ1995-1996 ዓ.ም በአፋር ክልል በስራና ከተማ ልማት ቢሮ በዲዛይን ቡድን መሪነት፣
- ከ1997-1998 ዓ.ም PSCAP በአፋር ክልል የከተማ ልማት ማሻሻያ ንኡስ ፕሮግራም አስተባባሪ፣
- ከ1999-2001 በGIZ የዩኒቨርሲቲ አቅም ግንባታ ፕሮግራም (UCBP) የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የግንባታ ፕሮጀክት ምክትል ስራ አስኪያጅና ከፍተኛ የሳይቱ ተቆጣጣሪ መሃንዲስ
በመሆን ግንባታው በተያዘለት ጊዜና ጥራት እንዲጠናቀቅ ስራውን በማስተባበር ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክተዋል፡፡
- ከ2003-2007 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ደግሞ የአፋር ክልል የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል፡፡
- ከ2008 ዓ.ም መጀመሪያ ጀምሮ በኢፌዴሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን በማገልገል ላይ ናቸው፣

በዚህም ጊዜ ውስጥ በክልል፣ በመንግስትና በተለያዩ የልማት አጋሮች የሚሰሩ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ስራዎችን በማስተባበር አደጋ ሲከሰት ፈጣን ምላሽ እንዲሰጥበት በማድረግ
ውጤታማ ስራ ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ በሌላ በኩል በክልሉ የሚሰሩ መንግስታዊ ድርጅቶችንና የልማት አጋሮችን በማስተባበር የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘቡ ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች
ተቀርፀው እንዲተገበሩ ሰርተዋል፡፡


የኢፌዴሪ የውኃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር

ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ

ብሔር፦ ኦሮሞ

የትምህርት ዝግጅት

- የመጀመሪያ ዲግሪ በሲቪል ምህንድስና፣
- የማስተርስ ዲግሪ በሃይድሮሊክስ ምህንድስናና ሃይድሮሎጂ ከኒውካስትል ዩኒቨርሲቲ ኢንግላንድ፣
- የፒ.ኤች.ዲ (PHD) በሃይድሮሊክስና በውኃ ሃብት ምህንድስና ከድሬስደን ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቴክኖሎጂ በከፍተኛ ማዕረግ፣

ዋና ዋና የስራ ልምዶች

- ከ1980-1996 ዓ.ም በቀድሞው የአርባ ምንጭ ውኃ ቴክኖለጂ ኢንስቲትዩት ከጀማሪ መምህርነት እስከ ዲንነት በተለያዩ ደረጃዎች የሰሩ ሲሆን የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
እስኪመሰረት ድረስ ምስረታውን በኃላፊነት መርተዋል፣
- ከ1996-2003 ዓ.ም አለም አቀፍ የውኃ ምርምርና አስተዳደር ኢንስቲትዩት (IWMI) የምስራቅ አፍሪካና የናይል ተፋሰስ ኃላፊ በመሆን አለም አቀፍ ሙያተኞችን
መርተዋል፡፡ በመጨረሻም የአፍሪካ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ሆነው ሰርተዋል፣
- ከ2003-2006 ዓ.ም የተ.መ.ድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክስ ኮሚሽን የውኃና የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ስፔሻሊስት ሆነው ሰርተዋል፣
- ከ2006 ዓ.ም እስከ አሁን የተ.መ.ድ ኒውዮርክ በኢኮኖሚና ሶሻል ዲፓርትመንት የ2030 ዘላቂ የልማት ግቦች የአቅም ግንባታ፣ የውኃና ኢነርጂ

ከፍተኛ ኢንተር ሪጅናል አድቫዘይር በመሆን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
ከ60 በላይ የምርምርና የማስተማሪያ መፅሃፍት በመፃፍና ፅሁፎችን በግልና በቡድን በታወቁ አለም አቀፍ ጆርናሎች ያሳተሙ በተለያዩ ሀገራዊና አለም አቀፍ ተቋማት ቦርዶችንና
የጥናት ቡድኖች የመሩ ያስተባበሩ በተለይም ደግሞ በውኃና በቴክኖሎጂ ዙሪያ የሚሰሩ ካውንስሎች አባልና አስተባባሪ በመሆን ሰርተዋል፡፡ ውኃን ማዕከል ያደረገ Think Thank
በመመስረት የጊቤ 3 ግድብ የብሄራዊ ኤክስፐርት ፓናል ም/ሰብሳቢ በመሆን ሰርተዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜም ኒውዮርክ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመሆን ሀገር ወዳድ
ኢትዮጵያውያን ምሁራን በማሰባሰብ በኢትዮጵያ የሳይንስና የሂሳብ ትምህርቶች ላይ ድጋፍ እንዲሰባሰብ በማድረግ ላይ የሚገኙ ከአገርና አህጉር አልፈው በአለም አቀፍ የፖሊሲና
ስትራቴጂ ንድፍ ስራ የሚያግዙ ምሁር ናቸው።

የማዕድን ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትር

አቶ ሞቱማ መቃሳ

ብሔር፦ ኦሮሞ

የትምህርት ዝግጅት

- የመጀመሪያ ዲግሪ በስታቲክስ (BSC) የትምህርት ዘርፍ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣
- በዚሁ የትምህርት ዘርፍ የሁለተኛ ዲግሪ (MSC) ከህንድ አገር ፓቲየላ ዩኒቨርሲቲ፣
- በተጨማሪ በውኃ ሀብት አስተዳደር፣ በኢነርጂ ዘርፍና በተመሳሳይ ዘርፎች ላይ በአለም አቀፍና አገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ጊዜያት በተካዱ ስልጠናዎች፣ ኮንፈረንሶችና ዎርክሾፖች
ላይ ተሳትፈዋል፡፡

ዋና ዋና የስራ ልምዶች

- ከ1980-1991 ዓ.ም በተለያዩ መ/ቤቶች በፕሎንና በጀት ስራ ከፍል ከጀማሪ ባለሙያ እስከ ከፍተኛ ባለሙያ በመሆን ሰርተዋል፣
- ከ1992-1997 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ውኃ ሃብት ቢሮ በፕላንና በጀት መምሪያ ኃላፊነት እንዲሁም በግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያኃላፊ ሆነው ሰርተዋል፣
- ከ1998-መጋቢት 2000 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የውኃ ሀብት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሰርተዋል፣
- ከግንቦት 2000-ህዳር 2001 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ በመሆን ሰርተዋል፣
- ከታህሳስ 2001-መጋቢት 2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ ፅ/ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ በመሆን ሰርተዋል፣
- ከሚያዚያ 2004-መስከም 2008 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል የውኃ፣ ማዕድንና ኢንርጂ ቢሮ ኃላፊ በመሆን ሰርተዋል፣
- ከጥቅምት 2008 እስከ አሁን የውኃ፣ መስና ኤሌሄክትሪሲቲ ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን እየሰሩ የሚገኙ ሲሆን
ከላይ በተዘረዘሩት የስራ ጊዜያት በተመደቡባቸው ቦታዎች ውጤታማ ተግባር ያከናወኑ ናቸው።


የኢፌዴሪ የአካባቢ፣ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር

ዶ/ር ገመዶ ዳሌ

ብሔር፦ ኦሮሞ

የትምህርት ዝግጅት

- የመጀመሪያ ዲግሪ (BSC) ባዮሎጂ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣
- ማስተርስ ዲግሪ (MSC) በእፅዋት ሳይንስት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣
- ፒ.ኤች.ዲ (PHD) በግብርና ሳይንስ ጂኦርግ ዩኒቨርሲቲ ጀርመን፣

ዋና ዋና የስራ ልምዶች

- በ1984 ዐ.ም የሁለተኛ ደረጃ መምህር፣
- ከ1985-1989 ዓ.ም የወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊ፣
- ከ1989-1992 ዓ.ም በኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የስልጠና ባለሙያ፣
- ከ1992-1993 ዓ.ም የዕ ፅዋት ሳይንስ ባለሙያ በመሆን በኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ጥበቃ ኢንስቲትዩት፣
- ከ1993-1995 ዓ.ም በቦረና የአርብቶ አደር ልማት ፕሮግራም ረዳት ተመራማሪ፣
- ከ1996-2003 ዓ.ም በዳይሬክተርነትና በክፍል ኃላፊነት በብዝሃ ህይወት ጥበቃ ኢንስቲትዩት ውስጥ ሰርተዋል፣
- ከ2004 ዓ.ም እስከ አሁን የብዝሃ ህይወት ጥበቃ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በመሆን የሰሩ ሲሆን፣

ሃያ አምስት የምርምር ፅሁፎችን በግልና በቡድን በታወቁ ጆርናሎች ያሳተሙ መሆናቸው በመምህርነት፣ በተለያዩ ቦታዎች ውስጥ በተመራማሪነት፣ በባለሙያነትና አመራርነት
አገልግለዋል።

የኢፌዴሪ የመንግስት የልማት ድርጅት ሚኒስትር

ዶ/ር ግርማ አመንቴ

ብሔር፦ ኦሮሞ

የትምህርት ዝግጅት

- የመጀመሪያ ዲግሪ (BSC) በፎረስትሪ ከአለማያ ዩኒቨርሲቲ፣
- ማስተርስ ዲግሪ (MSC) Production Forestry የስዊድሽ ግብርና ዩኒቨርሲቲ ከወንዶ ገነት ደን ኮሌጅ ጋር በመተባበር፣
- ፒ.ኤች.ዲ (PHD) In silvi-culture ከአልበርት ሊዲዊግስ ዩኒቨርሲቲ ጀርመን

ዋና ዋና የስራ ልምዶች

- ከ1988-1992 ዓ.ም በሞጆ የማገዶ እንጨት ተከላ ፕሮጀክት ባለሙያ፣
- ከ1993-1996 ዓ.ም የአዳባ ዶዶላ የተቀናጀ የደን ፕሮጀክት ባለሙያ፣
- ከ1997-1998 ዓ.ም የኦሮሚያ ክልል የደን ልማት ኃላፊ፣
- ከ1998-2000 ዓ.ም የኦሮሚያ የመሬት አጠቃቀም ም/ዳይሬክተር፣
- ከ2001-2003 ዓ.ም የኦሮሚያ የመንግስት ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ዳይሬክተር፣
- ከ2003-ነሃሴ 2007 ዓ.ም የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣
- ከ2007 መጨረሻ ጀምሮ የምስራቅ አፍሪካ ዩኒክ የደንና የመሬት አጠቃቀም ዳይሬክተር በመሆን እያገለገሉ ያሉ ሲሆን

ከ12 በላይ የምርምር ፅሁፎችንና ሪፖርቶችን በግልና በቡድን በአለም አቀፍ በታወቁ ጆርናሎች ያሳተሙ፣ የተለያዩ የአለም አቀፍ የእውቅና ሽልማቶችንም ያገኙ ከፍተኛ ባለሙያ፣
መምህርና አማካሪ ተመራማሪና በተለያዩ ደረጃዎች በአመራርነት አገልግለዋል።


የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስትር

ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም

ብሔር፦ሀዲያ

የትምህርት ዝግጅት

- በተቋማ አመራር የማስተርስ ዲግሪ፣
- በህብረተሰብ ጤና ሳይንስ የማስተርስ ዲግሪ፣
- በህክምና ትምህርት የዶክትሬት ዲግሪ፣

ዋና ዋና የስራ ልምዶች

- ከ1985-1998 ዓ.ም ድረስ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ኃላፊነትን ጨምሮ በተለያዩ ደረጃዎች መሰረታዊ ጤና አገልግሎቶችን በክልሉ በመዘርጋትና በማስፋፋት፣
- ከ1990-2000 ዓ.ም ድረስ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የፕሮግራም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን የምዕተ አመቱን የጤና ልማት ግቦችን በማሳካት፣
- ከ2001-2007 ዓ.ም ድረስ በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ልዩ ድጋፍ በሚሹ ክልሎች ተመጣጣይ ልማት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ፕሮግራሞችን በማቀድና በመተግበር፣
- በየአካባቢው በድንበር አካባቢ የሚታዩ የድንበር ግጭቶችን ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ ከሚመለከታቸው ጋር አብሮ በመስራት፣
- የኃይማኖት አክራሪነትና ፅንፈኝነትን ለመከላከል ማህበረሰብ ተኮር ንቅናቄ በማቀጣጠል፣
- የፌዴራል ስርዓቶች ግንባታ ግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም በመዘርጋት በትምህት ተቋማት ተግባራዊ በማድረግ፣
- ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን በአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ አለም አቀፍ ድርድሮችን
በማካሄድ የኢትዮጵያን መሪነት የማስቀጠል፣ የተለያዩ ሀብት የማፈላለጊያ ሰነዶች እንዲዘጋጅ በማድረግ የአገራችንን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ፣


የኢፌዴሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር

ፕ/ር ይፍሩ ብርሃነ

ብሔር፦ አማራ

የትምህርት ዝግጅት

- በህክምና ዶክትሬት ድግሪ፣
- የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ሀኪም፣
- የትምህርት ማዕረጋቸው የማህፀንና ፅንስ ፕሮፌሰር፣

ዋና ዋና የስራ ልምዶች

- የተለያዩ ፕሮጀክቶችና የጥናትና የምርምር ቡድኖችን የመራ፣
- ከ1989-1990 ዓ.ም የቡሌ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት ኃላፊ፣
- ከ1991-1992 ዓ.ም የዲላ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር፣
- ከ1998-2007 ዓ.ም የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት አባል የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን፣
- ከ2008 ዓ.ም መጀመሪያ ጀምሮ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኃላፊ፣
- ከ70 በላይ የምርምር ፅሁፎችን በግልና በቡድን በታወቁ ጆርናሎች ያሳተሙ ምሁር ናቸው፡፡

ከላይ በተጠቀሱት የትምህርት ዘርፍና በአመራር ዘርፍ በመሰማራት በጤና ልማትና ምርምር ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ በቅርቡ በተመደቡበት የጥቁር አንበሳ ሆስፒታልና ጤና
ሳይንስ ኃላፊነት ጉልህ ውጤት ማምጣት የጀመሩ ተመራማሪ፣ መምህርና ሀኪም ሆነው ሰርተዋል።


የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር

ዶ/ር ሂሩት ወ/ማርያም

ብሔር፦ ከምባታ

የትምህርት ዝግጅት

- የመጀመሪያ ዲግሪ (BA) ስነ ልሳን (የቋንቋና ጥናት)
- የሁለኛ ዲግሪ (MA) በስነ ልሳን (የቋንቋና ጥናት)
- ፒ.ኤች.ዲ (PHD) በስነ ልሳን ከኮለን ዩኒቨርሲቲ ጀርመን፣
- የአካዳሚክ ማዕረጋቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በስነ ልሳን ተባባሪ ፕሮፌሰር፣

ዋና ዋና የስራ ልምዶች

- ከ1981-1988 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አካዳሚ ተመራማሪ በመሆን አገልግለዋል፣
- ከ1989-1995 ዓ.ም የአዲስ አበባ ሌክቸረር፣
- ከ1998-2000 ዓ.ም የትምህርት ክፍል ኃላፊ፣ የዩኒቨርሲቲዎች የፀረ ሙስና መኮንን በመሆን፣
- ከ2000-2002 ዓ.ም ድረስ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ም/ፕሬዝዳንት፣
- ከ2002 እስከ አሁን ድረስ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣

ከ31 በላይ የምርምር ውጤቶችን በግልና በቡድን አለም አቀፍ ደረጃ በጠበቁ ጆርናሎች ያሳተሙ በርካታ አለም አቀፋዊ በሆኑ ኮንፈረንሶች ሀገራቸውንና የሙያ ዘርፋቸውን
በመወከል የምርምር ፅሁፎች በማቅረብ የሚታወቁ በአለም አቀፍ የምርምር ትስስር ውስጥ በቦርድ አባልነት የሚሰሩ ምሁር ሲሆኑ የሀገራችን የብሄረሰቦች ቋንቋዎች ጥናት በማድረግ
ከፍተኛ አስተዋፅኦ አላቸው።


የኢፌዴሪ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስትር

ወ/ሮ ደሚቱ ሃምቢሳ

ብሔር፦ ኦሮሞ

የትምህርት ዝግጅት

- የመጀመሪያ ዲግሪ በህግ ትምህርት (LLB) ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣
- ማስተርስ ዲግሪ በሊደርሺፕ ከግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ፣

ዋና ዋና የስራ ልምዶች

- ከ1975-1996 ዓ.ም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህርነት፣ በወረዳ ትምህርት ቤቶች ፅ/ቤት ስራ አስኪያጅነት፣ በምስራቅ ወለጋ ዞን የሴቶች ጉዳይ መምሪያ ኃላፊነት፣
- ከ2000-2005 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የአቃቤ ህግ ቢሮ አማካሪ፣ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የጥቃቅንና አነስተኛ ኤጀንሲ ኃላፊ፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት
ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ፣
- ከ2006-2007 ዓ.ም ድረስ የኤፌዴሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር፣
- ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የኢፌዴሪ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር፣
በመሆን ያገለገሉ ሲሆን ታታሪ፣ ጥሩ ስነ ምግባር ያላቸውና የተሰጣቸውን ኃላፊነት በብቃት፣ በታማኝነትና በቁርጠኝነት በመወጣት ውጤታማ ስራ በመስራት ላይ የሚገኙ አመራር
ናቸው፡፡


የኢፌዴሪ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር

አቶ እርስቱ ይርዳ

ብሔር፦ ጉራጌ

የትምህርት ዝግጅት

- የመጀመሪያ ዲግሪ በልማት አስተዳደር ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣
- ሁለተኛ ዲግሪ በከተማ አስተዳደር ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣

ዋና ዋና የስራ ልምዶች

- ከ1984-2001 ዓ.ም ከወረዳ እስከ ዞን አስተዳዳሪነት፣
- ከ2001-2002 በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሶማሌ ክልል የልማት አማካሪ፣
- ከ2003-2004 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የማህበራዊ ፖሊሲ አፈፃፀም ክትትል ሚኒስትር ዴኤታ፣
- ከ2004-2007 ዓ.ም በግብርና ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የሶማሌና አፋር ክልሎች ድጋፍ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ኃላፊ፣
- ከ2008 እስከ አሁን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላሰተር አስተባባሪና የንግድ ቢሮ ኃላፊ በመሆን፣

የኢፌዴሪ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ኃላፊ ሚኒስትር

አቶ ከበደ ጫኔ

ብሔር፦ አማራ

የትምህርት ዝግጅት

- የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በህግ (LLB) ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል፡፡
- የሁለተኛ ዲግሪያቸውን በሰላምና ደህንነት (Peace and Security) (MA) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል፡፡

ዋና ዋና የስራ ልምዶች

- ደርግን ለመደምሰስ በተደረገው የትጥቅ ትግል ከ1976 ዓ.ም ጀምሮ በተለያየ የኃላፊነት ደረጃዎች የተሰጣቸውን ተልዕኮ በታጋይነታቸው ተወጥተዋል፡፡
- ከ1983 ዓ.ም እስከ 1986 ዓ.ም የብአዴን የድርጅትና ፖለቲካ ዘርፍ አባልና ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል፡፡
- ከ1987 ዓ.ም እስከ 1993 ዓ.ም ድረስ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ካቢኔ አባልና የአቅም ግንባታና ሞቢላይዜሽን ዘርፍ ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል፡፡
- ከግንቦት 1997 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2004 ዓ.ም የክልሉ አስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል፡፡
- ከህዳር 1 ቀን 2004 ዓ.ም እስከ 2007 ዓ.ም የንግድ ሚኒስትር ሆነው ሰርተዋል፡፡
- ከ2008 ዓ.ም እስከ አሁን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የህዝብ ግንኙነት አማካሪ ሚኒስትር በመሆን እየሰሩ ያሉ ናቸው፡፡

ከላይ በተዘረዘሩት የስራ ቦታዎች ተመድበው በሰሩባቸው ጊዜያቶች ሁሉ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት የተወጡ በመሆናቸው፤ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ
እንዲከበርና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ ዋስትና እንዲያገኝ በትጋት ሰርተዋል፡፡ የንግድ አሰራርና ሪፎርሙ ውጤታማ እንዲሆን ሌት ተቀን የተጉና የንግድ ሪፎርም ፓኬጅ አዘጋጅተዋል፡፡

የኢፌዴሪ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ ሚኒስትር

ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ

ብሔር፦ ኦሮሞ

የትምህርት ዝግጅት

- የመጀመሪያ ዲግሪ (BA) በእንግሊዝኛ ቋንቋ እና ስነ ፅሁፍ ከኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ፣
- ማስተርስ ዲግሪ (MA) በሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ጥናት ከሃይአራባድ ዩኒቨርሲቲ ህንድ፣
- ፒ.ኤች.ዲ (PHD) በጋዜጠኝነትና በሚዲያ ኮሚዩኒኬሽን ከአንድራ ዩኒቨርሲቲ ህንድ፣
- የትምህርት ማዕረግ ረዳት ፕሮፌሰር በሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን፣

ዋና ዋና የስራ ልምዶች

- ከ1988-1993 ዓ.ም የምርምር ኤክስፐርት በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣
- ከ1996-1997 ዓ.ም በጋዜጠኝነት በቀድሞ የኦሮሚያ ኢንፎርሜሽን ቢሮ፣
- ከ1997-2002 ዓ.ም ሌክቸረርና ተጠባባቂ ዲን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣
- ከ2003 ዓ.ም እስከ አሁን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን ት/ቤት በድህረ ምረቃ አስተባባሪነት፣
- በአሁኑ ጊዜ ከመደበኛ ስራቸው በተጨማሪ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን የቦርድ አባል እንዲሁም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትና የኦሮሚያ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት
የቦርድ አባል በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

ከላይ የተዘረዘሩት የትምህርት ዝግጅትና የስራ ልምድ በመያዝ በሚዲያያ ኮሚዩኒኬሸንና በባህል ጉዳዮች ላይ ከሶስት በላይ መፅሃፍት ያሳተሙ የተለያዩ ህትመቶችን በታወቁ ጆርናሎች
ያሳተሙ፣ በተመራማሪነት፣ በመምህርት፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነትና የተለያዩ ከሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን የጥናትና የምርምር ስራ አከናውነዋል።
የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ

ብሔር፦ ኦሮሞ

የትምህርት ዝግጅት

- የመጀመሪያ ዲግሪ (BA) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካል ሳይንስና አለም አቀፍ ግንኙነት፣
- ማስተርስ ዲግሪ (MA) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአለም አቀፍ ግንኙነት፣
- ፒ.ኤች.ዲ (PHD) University of South Africa (UNISA) በፖሊሲ ሳይንስ አግኝተዋል፡፡

ዋና ዋና የስራ ልምዶች

- ከ1985-1991 ዓ.ም በብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች፣
- ከ1992-1993 ዓ.ም በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የፍትህ ቢሮ ኃላፊ፣
- ከ1994-2005 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር፣
- ከ2005 ሃምሌ እስከ አሁን የትራንስፖርት ሚኒስትር በመሆን፣

ከላይ በተዘረዘሩት ቦታዎች ባገለገሉባቸው ዘመናት የህዝቡንና የሀገሪቱን ሰላም የሚያስጠብቁ ስኬታማ ተግባራት በማከናወናቸው ዘመናዊና የፖሊስ ሰራዊት ግንባታ ሂደት ጠንካራ
አመራር የሰጡ፤ በትራንስፖርት ሚኒስትርነታቸው ዘመን የመንገድ መሰረት ልማት ስራዎች እንዲፋጠኑ የከተማና ሀገር አቀፍ የባቡር መሰረተ ልማት የመንግስት በሰጠው አቅጣጫ
መሰረት በተቀመጠላቸው ጊዜ እንዲሳኩ የበኩላቸውን ጉልህ የአመራር ድርሻ አበርክተዋል፡፡