1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
በአሮሚያ ክልል ህዝቡን ያስቆጡ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለማስወገድ መንግስት በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑ
ተገለፀ
December 12, 2016
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣
2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሮሚያ
ክልል ከተሞች ህዝቡን ያስቆጡ
የመልካም አስተዳደር እጦትና
የኪራይ ሰብሳብነት ችግሮችን
ለማስወገድ መንግስት
በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን
የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ
ለማ መገርሳ ገለጹ።

በክልሉ አዲስ ወደ ሃላፊነት
የመጡ የከተማ አመራሮች
ለህብረተሰቡ ተገቢውን
አገልግሎት መስጠት
በሚችሉበት አግባብ ዙሪያ
በአዳማ ከተማ አባ ገዳ
አደራሽ ስልጠና መስጠት
ተጀምሯል።
በስልጠናው መክፈቻ ስነሰርዓት ላይ ርዕሰ መስተዳደሩ እንደገለጹት፥ ከህዝቡ የተነሳው ቅሬታ ተገቢ ምላሽ እንዲያገኝ አመራሩን
መቀየር ብቻውን ግብ አይደለም።

አዲስ አበባ፣ ህዳር 06፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መንግስት በከፍተኛ አመራሩ የጀመረውን ጥልቅ ተሃድሶ እስከታችኛው የአመራር
እርከን ድረስ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ
ተናገሩ።

ሚኒስትሩ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ በከፍተኛው አመራር የተደረገው ብቃትን ያማከለ ለውጥ
በሁሉም ደረጃ እንዲቀጥል በማድረግ ከአመራር ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን መፍታት ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት
መሆኑን ተናግረዋል።

መንግስት የጥልቅ ተሃድሶ በማድረግ የትምህርት ዝግጅት፣ የስራ ተሞክሮ እና ውጤታማነትን መሰረት በማድረግ የካቢኔ ለውጥ
ማድረጉን ሚኒስትሩ አንስተዋል።

ይህ መታደስ ግን እስከታችኛው አመራር ድረስ ካልቀጠለ የይስሙላ ነው የሚሆነው፤ ስለዚህ የጥልቅ ተሃድሶ እስከታችኛው
የአመራር እርከን ድረስ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በክልሎች ከሰሞኑ እየተደረገ ያለው የተሃድሶ ግምገማም ለውጡን እስከታች የማውረድ ሂደት አካል ነው ሲሉም ዶክተር ነገሪ
ይናገራሉ።

ትክክለኛ መረጃ

ሚኒስትሩ አክለውም፥ በመንግስትና በህዝቡ መካከል ፈጣን የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር በማድረግ የህዝብ እና የመንግስትን
ግንኙነት ይበልጥ የማጠናከር ስራ እንደሚሰራም ነው የገለፁት።

በመንግስት በኩል መረጃን በፍጥነት የመስጠት ችግር አለብን ያሉት ሚኒስትሩ፥ የችግሩ ምንጭ ወደ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን
ጽህፈት ቤት ቶሎ መረጃን ያለማድረስ እንዲሁም የተገኘው መረጃም ቢሆን ጥራት የሌለው እና የተሸፋፈነ መሆኑ ነው ይላሉ።

በመሆኑም በቀጣይ እያንዳንዱ የህዝብ ግንኙነት ስለ መስሪያ ቤቱ በቀጥታ መረጃን እንዲሰጥ ይደረጋል፤ ከዚህ ባለፈ ግን
ዋና ዋና ጉዳዮች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አማካይነት እንዲሰጥ ይድረጋል ነው ያሉት።

ለህዝቡም መረጃ ያለምንም ችግር በቀጥታ የሚደርስበትን ሁኔታ እናመቻቻለን ሲሉም ዶክተር ነገሪ ተናግረዋል።

ለበርካታ አመታት በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ላይ ጥናት እና ምርምር ያደረጉት ዶክተር ነገሪ፥ በታዳጊ ሀገራት የሚኖር
ህዝብ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ድህነት ውስጥ የሚኖር ነው ይላሉ።

“ከፍተኛ የኢኮኖሚ ድህነት እና ያልዳበረ ዴሞክራሲ ባለበት ሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን የህዝቡን ነባራዊ ሁኔታን
በትክክል የሚገልጽ መረጃ ሊሰጡ ይገባል፤ ይሁንና ባካሄድኩት ጥናት ጋዜጠኛው ታች ድረስ ወርዶ የህዝቡን ጥያቄ ይዞ ሲመጣ
የመንግስትን በጎ ስም ያጠፋል በሚል ምክንያት ዜናውን የሚጥሉ ሚዲያዎች አሉ” ብለዋል።

“ይህ ደግሞ ጋዜጠኛውን ከምርመራ ስራዎች ይልቅ የስኬት ዜና ለመስራት እንዲገደድ ያደርጋል” ሲሉም ዶክተር ነገሪ
አስታውቀዋል።

“በዚህ ጊዜም ህዝብም ማግኘት ያለበትን መረጃዎች እንዲያጣ ይደረጋል፤ በመንግስት እና በህዝብ መካከል የተፈጠረውን
ክፍተት ደግሞ ጽንፈኞች በአግባቡ የቤት ስራቸውን ይሰሩበት እና የህዝብ ድምጽ በሌላ መንገድ እንዲገለጽ እድል ይፈጥራል”
ባይ ናቸው።

በቀጣይ ይላሉ ዶክተር ነገሪ፥ “መረጃዎች በትክልል ለህዝብ የሚደርሱበት አሰራር ይዘረጋል፤ እንዲሁም በፌደራልም ሆነ
በክልል ደረጃ ለመገናኛ ብዙሃን አካላት አቅምን የመገንባት ስራ ይከወናል” ብለዋል።

“ትክክለኛ እና በአፋጣኝ መረጃን የማይሰጡ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ተጠያቂ የሚሆኑበት አሰራር ይዘረጋል” ሲሉም
ገልጸዋል።

መንግስት መረጃን አፍኖ የመያዝ ችግር አለበት የሚል ጥያቄ የተነሳላቸው ሚኒስትሩ፥ “በመጀመሪያ መንግስት መረጃን
የማፈን መብት የለውም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“መረጃን የማፈን ፍላጎት ቢኖረው ኖሮ ቀድሞውኑ መብቱን አይፈቅድም ነበር፤ ነገር ግን አሁን በሀገሪቱ የሚታየው ችግር
መብቱ ተሰጥቶ ሳለ በህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ዘንድ መረጃን በመደበቅ፣ አለቃን የማስደሰት ፍላጎትና የስኬት ዜናዎች
ብቻ እንዲወሩ መፈለግ ናቸው የችግሮቹ ምክንያቶች” ይላሉ።

በመሆኑም ይህን ችግር ለመፍታት ግልጽ የሆነ የአሰራር መንግድ መቀየስ አስገዳጅ ይሆናል ሲሉም ተናግረዋል።


በብስራት መለሰ
admin@hebrezema.info
1