1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
ወደ ኢትዮጵያ የተዘረጉ ስውር የግብፅ እጆች በኢትዮጵያውያን የጋራ ትብብር ሊመከቱ ይገባል -
ምሁራን
October 26, 2016
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2009 (ኤፍ.
ቢ.ሲ) ወደ ኢትዮጵያ የተዘረጉ ስውር
የግብፅ እጆች በኢትዮጵያውያን የጋራ
ትብብር ሊመከቱ እንደሚገባ ምሁራን
ይናገራሉ።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው
የቀጠናዊ ፖለቲካ ጉዳዮች ልሂቃን ግብፅ
በተለያዩ ስልቶች ኢትዮጵያን የማፈራረስ
አላማ ካላቸው ሀይሎች ጋር እየተባበረች
መሆኗን ተናግረዋል።

የግብፅ ስጋት እና ሴራ

ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያ
እያስመዘገበች በመጣው የምጣኔ ሀብት
እድገት ክፉኛ ካስደነገጣቸው ሀገራት
ቀዳሚዋ ግብፅ መሆኗን ለመናገር ብዙ
ማሰብ ማሰላሰል አያስፈልግም ይላሉ
የዚያችን ሀገር ጂኦ ፖለቲካዊ ጉዳዮች
የሚከታተሉ ፀሃፍት እና የፖለቲካ
ምሁራን።
ለምን ግብፆች ከዘመነ ፈርኦን እስከ 21ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ኢትዮጵያ ከተጠናከረች እስትንፋሳችን የሚሉት
የአባይ ውሃ ይቀንሳል የሚል አቋም በመያዛቸው።

ይህ ስጋታቸው ደግሞ ከመቼውም ጊዜ በላይ አሁን ላይ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል።

ለምን? ኢትዮጵያ በርካታ ፈተናዎችን አልፋ ባለፉት ዓመታት ተከታታይ የምጣኔ ሀብት እድገት ማስመዝገብ
በመቻሏ።

እናም የኢትዮጵያን ዘርፈ ብዙ እድገት ተከትሎ የካይሮ ሴራዎችን አቅጣጫዎችን እየቀያየሩ መምጣት ጀመሩ።

በተለይ የታላቁ ህዳሴ ግድብ የግንባታ መሰረት ከተጣለበት ዓመት ጀምሮ ካይሮ አዲስ አበባ ውስጥ የሚነደፉ
የኢኮኖሚ እቅዶችን፣ ትላልቅ መሰረተ ልማት አውታሮችን በጥንቃቄ ማጥናት ጀመረች።

ካይሮ በአዲስ አበባ ላይ የጥፋት ሴራዎቿን የረዥም ጊዜ ህልሞቿን ለማሳካት ሁለት መንገዶችን ለመጠቀም
እየሞከረች ነው።

በጅማ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና የልማት ጥናት ትምህርት ክፍል ባልደረባ የሆኑት አቶ ኢድሪስ የባ ሁለቱን
የጥፋት መንገዶች ያብራራሉ።

አንደኛው በምሁራኖቿ በኩል የሚጎነጎነው የሚሸረበው ሴራ ነው፤ እነዚህ ስልቶች ደግሞ ታሪካዊ ስህተት ያለባቸውን
ታሪካዊ ስምምነቶንን ያጣቅሳሉ።

ግብፅ ከሱዳን ጋር በ1951 የገባችውን ስምምነት እያጣቀሱ የዛሬዎቹ ፖለቲከኞች ግፊት እንዲያደርጉ ይሯሯጣሉ፤ ይህ
ስምምነት ደግሞ የአባይ ወንዝ ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ ያልተሳተፈችበትና ዜጎቿን የማይወክል ነው።

ስምምነቱ ለኢትዮጵያ አንዳች እንጥብጣቢ ውሃ ከአባይ እንዳትጠቀም የሚያደርግ ሲሆን ምሁራኖቿ ግን ስምምነቱ
የያዘውን አጀንዳ እያነሱ አሁን ድረስ በርካታ ግብፃዊያን ለተንኮል እንዲነሱ እያደረጉ ነው።

ታላቁ የህዳሴ ግድብ

አቶ ኢድሪስ የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ለካይሮ ሌላኛው ራስ ምታት የሆነ ጉደይ መሆኑን አንስተዋል።

በርካታ ግብፃዊያን የዚህ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ በቀጣይ የኢትዮጵያን መጠናከር እና የህዝቡን አንድነት ለሌላ
የልማት አጀንዳ የሚያስተባበር አድርገው መመልከት ጀምረዋል ይላሉ ምሁሩ።

በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና የስትራቴጂክ ጉዳዮች ትምህርት ክፍል ሃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር መረሳ
ጸሃዬም ግብፆች የግድቡ ግንባታ እየተፋጠነ መሆኑን ሲያዩ ሌላ የስጋት ነፋስ ነፍሶባቸዋል ብለዋል።


ለመሆኑ ኢትዮጵያ አሁን ላይ ያለችበት አካባቢያዊ የጂኢ ፖለቲካ ሁኔታዎች ለግብፅ ስውር
እጆች ምን ያህል ምቹ ናቸው?

ግብፅ እና ኢትዮጵያ በመካከላቸው ያለውን ታሪካዊ እና አሁናዊ የአባይ ወንዝ የልዩነት ነጥቦች የሚከታለሉ የዘርፉ
ምሁራን ኢትዮጵያዊያን ካልተጠነቀቁ ነገሮች አስቸጋሪ ናቸው ይላሉ።

ለዚህም ኢትዮጵያ ባልተረጋጋው እና እዚህም እዚያም የፖለቲካ ትኩሳት የሚታመሱ የአሸባሪ ቡድኖች መንቀሳቀሻ
ቀጣና ውስጥ መገኘቷን በምክንያትነት ይጠቅሳሉ።

አዲስ አበባ መረጋጋት ባልሰፈነበት የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ውስጥ መገኘቷ የግብፅ ሴራ አቅጣጫ ብዙ ሆኖ
ሊመጣባት ይችላል ይላሉ።

ረዳት ፕሮፈሰሩ መረሳ ፀሃዬ ኤርትራ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን ውስጥ ያለው የፖለቲካ ትኩሳት በዋናነት የካይሮ
ሴራ መጠቀሚያ ሊሆን ይችላል ነው የሚሉት።

በእርግጥ አሸባሪ ቡድኖችን የሚረዳው እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሳይቀር ክፉኛ የሚወገዘው የማዕቀብ ሰለባ
የሆነው የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የአስመራው መንግስት የካይሮን ጥቅም ለማስጠቅቅ ወደኋላ አይልም።

የኤርትራ መንግስት በጥቅም ተደልሎ ወታደሮቹን የመን እያዋጋ መሆኑ ለዚህ ማሳያ አድርገውታል ረዳት ፕሮፌሰሩ።

ኢትዮጵያዊያን በአሁኑ ወቅት የግብፅን ሴራ እንደ በፊቱ መመልከት የለባቸውም፤ ምክንያቱም ዛሬ ላይ የኢትዮጵያ
እድገት ተጠናክሯል፤ የግብፅም ሴራ በዚያው ልክ እየተቀያየረ ነው ብለዋል ምሁሩ።

የጅማ ዩኒቨርሲቲው መምህር ኢድሪስ የባ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ማወቅ ያለበት ነጥብ በሀገራት ጣልቃ የሚገቡ የውጭ
ሃይሎች ተንኮላቸውን የሚያስፈፅሙት ዲሞክራሲያዊ ጥያቄዎችን ለመደገፍ በሚል ነው ይላሉ።

አቶ ኢድሪስ በፖለቲካ ሳይንስ ዴሞክራሲ የሚያብበው በውስጥ ጥንካሬ እንጂ በውጭ ጣልቃ ገብነት አለመሆኑንም
ገልፀዋል።

ረዳት ፕሮፌሰር መረሳ ፀሃዬ በበኩላቸው ዜጎች ግብፅ አሁን ላይ በኢትዮጵያ የምታካሂደውን አፍራሽ ድርጊት ብቻ
ሳይሆን ለነገም መጠንቀቅ አለባቸው ብለዋል።

ነገን መተንበይ የሚቻለው እና ሊፈፀም የሚችል አፍራሽ ድርጊትን በአጭሩ መቀልበስ የሚቻለው የሴራዎችን ምንጭ
ማወቅ ሲቻል ነው ባይ ናቸው ረዳት ፕሮፌሰር መረሳ።

ምሁራኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሀገሩ ህልውና መደራደር የለበተም የሚል አስተያየታቸውንም ሰጥተዋል።በስላባት ማናዬ
admin@hebrezema.info
1