1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
admin@hebrezema.info
የገዳ ስርዓት በዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች መዝገብ ላይ ሰፈረ
November 30, 2016

የኦሮሞ ብሄረሰብ ባህላዊና ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር የሆነው የገዳ ስርዓት በዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች መዝገብ ላይ
ሰፈረ፡፡
1
የገዳ ስርዓት በዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች መዝገብ ላይ እንዲሰፍር የተደረገው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ)
ዛሬ ባካሄደው 11ኛው የማይዳሰሱ ቅርሶች ጉባኤ ላይ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባህል ማዕከል ዋና ዳይሬተር ዶ/ር እልፍነሽ ሃይሌ በዚህ ወቅት እንዳሉት ገዳ ስርዓት በአገሪቷ የዴሞክራሲ ስርዓት ባልተዘረጋበት ወቅት
ዴሞክራሲን ስላማዊ ስልጣን ሽግግርን ያስተዋወቀ በመሆኑ በዩኔስኮ ሊመዘገብ ችሏል፡፡

የገዳ ስዓ በዩኔስኮ መመዝገቡ መልካም አጋጣሚ ሲሆን ባህሉ አንዲለማ እንዲጠበቅና ለትውልድ እንዲተላለፍ ሁላችንም ጠንክረን ልንሰራ ይገባልም ብለዋል፡፡

ዶ/ር እልፍነሽ በገዳ ስርዓት ብቻ ሳይሆን በሌላውም ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ ለሠላም፤ ለፍቅር፤ ለአንድነትና ለአብሮነት አስተዋጽኦ ያላቸው እሴቶችን ጠብቆ
ለትውልድ በማስተላለፍ ለዓለም ህዝብ መልካም ተሞክሮ ለማድረግ ጥረት ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡
የገዳ ስርዓትን ጨምሮ 37 አዳዲስ የማይዳሰሱ ቅርሶች በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገቡ ጥያቄ ቀርቦ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 11ኛው የዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች ጉባኤ የተለያዩ ሀገራት ወካይ ቅርሶችም በአለም ቅርስነት ተመዝግበዋል።

በፖርቹጋሉ የቢሳልሄዝ ጥቁር ሸክላ የማምረት ሂደት፣ በኡጋንዳ ማዲ የተሰኘ የሙዚቃ እና ዳንስ ትርኢት፣ በዩክሬን የኮዛኮች ሙዚቃዊ ትርኢት እንዲሁም
በካምቦዲያ የቻፓይ ዳንግ ቬንግ የሙዚቃ ባህል በዚህ አመት ዩኔስኮ አደጋ ላይ እንደሆኑ ተለይተው በአደጋ መዝገብ ሰፈረዋል።

10ኛው ጉባዔ አምና በናሚቢያ ሲካሄድ ኢትዮጵያ ፍቼ ጫምባላላን ማስመዝገቧ የሚታወስ ነው።

የዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች ኮንቬንሽን በ2003 የወጣ ሲሆን ኢትዮጵያ ኮንቬንሽኑን በ2006 መፈረሟ አይዘነጋም።

11ኛው የዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች ጉባኤ እስከ መጪው አርብ በአዲስ አበባ መካሄዱ ይቀጥላል።

http://www.ebc.et/