1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
በከተሞች መስፋፋት የተነሳ በአርሶ አደሮች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ ችግሮችን የሚፈታ ሰነድ ተዘጋጀ
October 31,2016
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በከተሞች የጎንዮሽ መስፋፋት በአርሶ አደሮች ላይ ሊደርሱ
የሚችሉ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች እንደሚፈታ የታመነበት ሰነድ ተዘጋጀ።

የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ዋና ዳሬክተር አቶ አባይ ፀሀዬ፥ በስድስት ከተሞች በናሙናነት በመውሰድ በተደረገ
ጥናት የተዘጋጀው ሰነድ ከከተሞች መስፋፋት ጋር በተያያዘ በህዝቡ ዘንድ የሚፈጠሩ ቅሬታዎችን የሚፈታ ነው
ብለዋል።

የተዘጋጀው ስነድ ከዳበረ በኋላ በስትራቴጂ፣ በህግና መመሪያ ተደግፎ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ተግባራዊ
ይደረጋል።

የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል በአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ መቀሌ፣ ሃዋሳና ጅማ በልማት
ከይዞታቸው ለሚነሱ ስዎች ያለው አሰራርና የአገልግሎት አስጣጥ ችግሮችን የተመለከተ ጥናት አካሂዷል።

በከተሞቹ ከይዞታቸው የሚነሱ ግለሰቦች የሚሰጥ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ፣ የካሳ ግምትና ክፍያ እንዲሁም
የመልሶ ማቋቋም ችግሮች መኖራቸው በጥናት ተረጋግጧል።

የማዕከሉ ዋና ዳሬክተር አቶ አባይ ፀሐዬ ጥናት ተደርጎ የተዘጋጀው ስነድ ከከተሞች መስፋፋት ጋር ተያይዞ
የሚፈጠሩ ችግሮችን በዝርዝር በመለየት የህዝቡን ቅሬታ ይፈታል ብለዋል።

ሰነዱ ከመሬት ይዞታቸው የሚነሱ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች በአካባቢያቸው ከሚከናወኑ የልማት ሰራዎች
ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አሰራርም ያመላክታል ነው ያሉት።

የተዘጋጀው ስነድ የከተሞችን የተመጣጠነ ዕድገት ማምጣት የሚያስችልና ከተሞችም የመሬት አጠቃቀማቸውን
በማሳደግ ለነዋሪዎቻቸው በርካታ መኖሪያ ቤት ማቅርብ የሚያስችል ሰልት እንዲከተሉ የሚያደርግ መሆኑንም
አንስተዋል።

ከተሞች ወደ ገጠር መውጣት የሚኖርባቸው በውስጣቸው የያዟቸውን ክፍት ቦታዎች በአግባቡ ከተጠቀሙ በኋላ ሊሆን
እንደሚገባው በጥናቱ ተጠቅሷል።

የማዕከሉ የከተማ ዘርፍ ተመራማሪ ዶክተር ዘመንፈስ ገብረእግዚያብሔር በበኩላቸው፥ በተደረገው ጥናት በልማት
ከይዞታቸው ለሚነሱ አርሶ አደሮች በቂ የካሳ ክፍያ መክፈል ብቻ የመጨረሻው ግብ መሆን እንደሌለበት ታይቷል
ብለዋል።

አርሶ አደሩ ወደ ከተሜነት ሲቀላቀል የኢኮኖሚ ስርዓቱ የሚቀየር በመሆኑ መልሶ የማቋቋም ክህሎትና በትንሽ ቦታ
ላይ ዘመናዊ ግብርና ማከናወን የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች መፍጠር ያሻል ነው ያሉት ዶክተር ዘመንፈስ።

ሰነዱ አሁን የሚስተዋሉና በቀጣይ ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ታሳቢ ያደረገ መሆኑንም ነው ተመራማሪው የገለጹት።

በተለይም በፖሊሲ፣ በስትራቴጂና በህግና መመሪያ ያሉ ክፍተቶችን በማሻሻል በዘርፉ የሚስተዋሉ ዋና ዋና ችግሮችን
ይፈታል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል።

የተዘጋጀው ስነድ በቀጣይም በባለድርሻ አካላት ዳበሮ መንግስት ለሚያደርጋቸው ማሻሻያዎች እንደሚያገለግል ይጠበቃል
admin@hebrezema.info
1